ሰላም ጤና ይስጥል ን የቻናላችን ቤተሰቦች ዛሬ ሁላችንም ማለትም አብዛሀኛወቻችንን ስለሚዳስስ ነገር ሽክ ልበላችሁ!!!ስልክዎን በመነካካት ሱሰ ተጠምደዋል፤ መፍትሄውን ጀባ እንበልዎ
_________________________________________________
በስልክዎ ማለቂያ አልባ ይዘት (content) ተውጠው ያውቃሉ? በተደጋጋሚስ ስልኮትን ይነካካሉ? አንዳቸውም የእርስዎ
ጥፋት አለመሆኑን ብንነግርዎስ፤ ይልቁንም ስልኮችዎ እንዲህ እንዲያደርግዎት ታስበው ነው የተሰሩት፡፡ በኪሶቻችን
ውስጥ ስላሉት ስለእነዚህ ኃይለኛ መሣሪያዎች ንድፍ (አሰራር) የበለጠ ባወቅን መጠን በጤንነት፣ ግንኙነታችን እና
በወደፊቱ ስኬታችን ላይ እንዴት ተፅእኖ እንደሚፈጥሩ ለመቆጣጠር የበለጠ እንረዳለን።
ስልካችን እንዴት ነው የተነደፈው? እኛስ ምን ማድረግ አለብን?
ስልኮቻችን የተሰሩት የእኛን ስነ-ልቦና በመከተል ስለሆነ ትኩረታችንን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ በትክክል ያውቃሉ፡፡
ታድያ ስልኮቻችን ሱስ እንዲያስይዙን ተደርገው ነው የተሰሩት? ስልኮቻችንን መልሰን መቆጣጠር እንችላለን?
በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስልኮቻችን እንዴት ጊዜያችንን ለመውሰድ እንደተፈጠሩና እኛም ማድረግ የምንችላቸውን ጥቂት
ቀላል እርምጃዎችን እንማራለን፡፡
፩. ማሳወቂያዎች (notifications) እንዳይደርሱን ማድረግ፤
በህይወታችን አስፈላጊ ከሆኑ ሰዎች በስተቀረ ለሌሎቹ ምላሽ አይስጡ፡፡ ሁሉንም ዜናዎች በተከሰቱበት ቅፅበት ማወቅ
ምን ያደርግልዎታል? ሁሉንም ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት በቀን የተወሰነ ጊዜ መመደብ ብቻ በቂ ነው፡፡
፪. የስልክዎን ብርሀን ያደብዝዙ፤
በእይታችን ውስጥ የገቡ ቀለም እና ምልክቶች ትኩረት እንድንሰጣቸው ያነሳሱናል፡፡ ስለሆነም ቀለማቱን ከሰወርን አዕምሮአችንን ወደ ስልከላችን የሚማርክ ምንም ነገር አይኖርም፡፡

December 16, 2019
Forwarded from አዛኝ፣ ትሁት፣ ተጫዋች፣ኮስታራ፣ አኩራፊ፣ቆራጥ ፣ ሳቂታ፣ ቶሎ ተስፋ ቆራጭ፣ ሲከፋው ዝምታን መራጭ፣ Www.habtechzone.blogspot.com
፫. የመነሻ ገጽዎን (home screen) ያስተካክሉ፤
በዚህ ተግባር ውስጥ ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ጠቃሚ የሆኑትን መተግበሪያዎችን (የቀን መቁጠሪያ፣ አድራሻዎች፣
ካርታ፣ የባንክ አገልግሎት…) ብቻ በማቆየት ሌሎቹን ከመነሻ ገጽዎ ያንሷቸው፡፡ እነዚህ ያነሳችዋቸው የማህበራዊ ሚዲያ
እና ሌሎች መተግበሪያዎችን በመሰብሰብ በቀላሉ ሊያገኟቸው በማይችሉበት ቦታ ያስቀምጡ፡፡
፬. ስልክዎን በቀላሉ በማይደርሱበት ስፍራ ያስቀምጡ፤
ይህ ቀለል ያለ መፍትሄ ነው፤ ስልክ ከጎንዎ ከሌለ ጊዜዎትን ሊወስድ አይችልም።
፭. ሱስ የሚያስይዙትን እነዚህን ባህሪያትን ለበጎ የሚጠቀሙ መተግበሪያዎችን ያውርዱ፤
ጤናማ ባህርያት ወይም ልምዶችን እንድናዳብር የሚያግዙን የሚያግዙ ብዙ መተግበሪያዎች አሉ፡፡ እነዚህን አይነት
መተግበሪያዎች ማህበራዊ ትስስርን የሚያበረታቱና ጤናማ አኳን እንዲኖረን የሚያደርጉ ናቸው፡፡
በመጨረሻም ቴክኖሎጂ አይቆጣጠርዎት እርሶ ይቆጣጠሩት እንጂ፤
ቴክኖሎጂ በጣም ጥሩ ነው በመሠረቱ በሕይወታችን ውስጥ የበለጠ እንድንሰራ ለማገዝ የተፈጠረ ነው:: የመጀመሪያው
አላማው ጊዜያችንን ሙሉ በሙሉ ማባከን አልነበረም:: ግን የስልኮቻችን አሰራር በእኛ ላይ እንዴት ተጽዕንዎ
እንደሚያሳድር ሁላችንም ብዙ እናውቃለን እናም ይህንን አውቀን ወደፊት ለመሄድ እና እድገትን እንዲያመጣልን
ቴክኖሎጂን መልሰን ልንቆጣጠረው ይገባል፡፡
ምንጭ- Ever Widening Circles

No comments:
Post a Comment