ዲሽ መግጠሚያ መሳሪያዎችና አጠቃቀማቸው


                         
                                        @በሙለር አይቲ ሶሱሽንስ ተዘጋጅቶ በሀብ ቴክኖሎጅ ሴንተር የቀረበ
ጀማሪ ወይም ልምድ ያላቸው ቴክኒሺያኖች መያዝ የሚገባቸው የሳተላይት ዲሽ መግጠሚያ መሳሪያዎችና አጠቃቀማቸው፡- - ማንኛውም የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሺያን በቅድሚያ የሚገጥመውን የሳተላይት ዲሽ አይነትና አቅጣጫ በአትኩሮትና በበቂ ሁኔታ ከምንም በላይ መገንዘብ ይኖርበታል፡፡ ዲሽ ጀማሪም ሆነ የተካነ ቴክኒሺያን ማወቅ ከሚገቡን ነገሮች መካከል የእያንዳንዱን ቻናል አቅጣጫና አቀማመጥ ነው፡፡ እነዚህን ቻናሎች በአግባቡ ለመትከል እንዲረዳን የአቅጣጫ ጠቋሚ ማለትም ኮምፓስ መጠቀም በብዛት የሳተላይት ዲሾችን ለመግጠም ጥቅሙ እጅግ ከፍ ነው፡፡ - የሳተላይት ዲሽ ለመትከል የተዘጋጀ ሰው መያዝ ያለባቸው እጅግ መሰረታዊና መሳሪያዎች 1. በተለምዶ አስር ቁጥር ብለን የመንጠራው የብሎን መፍቻ ለባለ 60 ሴንቲሜትር ሳህንና (ለ 90 ሲንቲሜትርና ከዛ ክፍ ለሚሉ የዲሽ ሳህኖች፣ 10 ቁጥርን ጨምሮ እንደአስፈላጊነቱ 10፣11፣12፣ እና ከዚያ በላይ ያሉት መፍቻዎች በተናጠል ወይም (በህብረት) ማለትም በአንድ የብረት ዘንግ ሶስቱንም በስሩ የያዘ መፍቻ ወይም ከአነስተኝ እስከ ከፍተኛ የብሎን አናት ቁጥሮችን በማጥበቅና በማላላት የምንጠቀምበት በተለምዶ ካበ እንግሊዝ (Wrench) ብለን የምንጠራውን ባለ አንድ ወጥ በጣት በማሽከርከር እንደ ብሎኑ አናት መጠን የሚጠብና የሚሰፋ መፍቻ 2. የሚቻልና አቅማችን ከፈቀደ ዲጂታል የሆነ የሳተላይት ማሰሻ ወይም Finder መግዛት 3. ከ ፋደራችን አይነትና አቅም ጋር የሚሄድ ተወርዋሪ ገመድ ከዲሹ ጋር ከሚመጣው RG-6 Coaxial Cable (የዲሽ ገመድ) ወይም ከቴሌቪዥን የውጭ አንቴና ጋር ከሚመጡ በውስጣቸው ቀጭን የኮፐር ወይም መዳብ ዘንግ ከያዙ ገመዶች ቆርጦ ርዝመቱ ከ 60 ሳንቲሜትር ያላነሰ ተወርዋሪ ገመድ (Jump Caple) በሁለቱም በኩል የሴቴ ወይም (Female Connector) የያዘ ገመድ ማዘጋጀት፡፡ የገመዱ ጫፍ አንደኛው ወደ የዲሹ ጭንቅላት (LNB) ላይ የሚታሰር ሲሆን ሌሌኛው ጫፍ ፋይንደሩ ላይ (To LNB) በሚለው አቅጣጫ የሚታሰር ይሆናል፡፡ 4. ተወርዋሪ ገመድ ወይም ከዲሹ ጋር አብሮ የሚመጣውን ገመድ ጫፎች ለመላጥ፣ Female Connector ችን ለማያያዝ፣ ገመዶችን ለማሳጠር ወይም ለመቀጠልና ለማስረዘም እንዲረዳን አንድ ጥሩ የሆነ ፒንሳ ያስፈልገናል፡፡ 5. የዲሹን LNB ማቀፊያ ለማጥበቅና ለማላላት ብሎም LNB ለመቀየርና አዳፕተሮችን ለመፈታታትና ለማጥበቅ ሊረዳን የሚችል በሁለቱም በኩል ሲቀያያር ጠፍጣፋና ባለ መስቀል አናት የሚሰጥ ካቻቢቴ መያዝ ይጠበቅብናል፡፡ 6. የዲሹን ሳህን እግር በሁለት አቅጣጫ ረዘም ካሉ ጣውላዎች ጋር መምቻና የዲሹን ገመዶች በየግድግዳው በኬብል ክሊፕ ለማያያዝና ሌሎች ጠንከር ያለ ሀይል የሚጠይቁ ስራዎችን ለማከናወን የሚጠቅመንን አጠርያለ የፕላስቲክ እጀታ ያለው መዶሻ ያስፈልገናል፡፡ • በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን ሊጠቅሙን ስለሚችሉ በርከት ያሉ የ Female connector, Audio Video Splittor Conector ንና ከሁለት ያላነሱ Disqe Switch መያዝ፡፡ • እንደየ ፍላጎታችን የምንሞላውን የተለያዩ ፊሪክዌንሲዎችና፣ ፖላራይዜሽሮች ዝርዝር በጥንቃቄ ለማወቅ ይረዳን ዘንድ እና አዳዲስ መረጃዎችን በማይረሱ መልኩ ለመፃፍና በአስፈላጊ ጊዜ ዋቢ ለማድረግ ለመፃፊያነት የሚረዱን ማስታወሻ ደብተሮችን •ተንቀሳቃሽ ስልኮችን መያዝ፡፡ የስማርት ስልከ መያዝ ወቅቱ ያፈራቸውን መረጃዎች በአቅራቢያችን እንዲኖሩንና ሌሎች ተጨማሪ ነገሮችን ያለ ብዙ ድካም ለማግኘት ስለሚረዱን በጥንቃቄ መያዝ • አንድ ባለ አንድ አውትፑት (ገመድ ተቀባይ) LNB እና አንድ ባለ ሁለት አወትፑት LNB ዎች ብንይዝ ለስራ በምንጓጓዝበት ወቅት የተቃጠሉ፣ ጉዳት የደረሰባቸውን፣ የደከመ የምስል ጥራት የሚያወጡ LNB ዎችን ለመለየትና በምትኩ በመግጠም ከአላስፈላጊ ድካምና ወጪ ራሳችንን ማዳን እንችላለን፡፡ • ከ20 ሜትር ያላነሰ የዲሽ ገመድ ለአያያዝ አመቺ በሆነ መልኩ መያዝ፡፡ • ነፃ የኳስ ቻናሎችን ወይም ሁለት LNB የሚጠይቁ ስራዎችን ለመስራት ዘንግ (የገበያ ስሙም ዘንግ ነው) መያዝ፡፡ • በተለያዩ ቦታዎች ለማጠናከሪያነት ሊጠቅሙን የሚችሉ የተለያዩ አይነት ሚስማሮችን መያዝ፡፡ •የገመድ ክሊፖች መያዝ፡፡ •ሜትር፡፡ • የተጠቀለለ ሽቦ መያዝ፡፡ • የዲሽ አሰሪ አካል ትብብር መጠየቅ (ብዙ ጊዜ እጅግ ያረጁና አጠቃቀማቸው ግራ የሚያጋባ ሪሲቨሮች ይገጥሙናል በዚህ ጊዜ ማድረግ የሚገባን አንድ ነገር ቢኖር መጀመሪያ ሲቀጥል እንደየ እድሜያቸውና እንደኛ አቅም፣እና እንደየ ፋብሪካ ስሪታቸው የሪሲቨሮቹን አሰራር መረዳት ሲሆን ብዙዎቹ ቆየት ያሉ ሪሲቨሮች በመጠኑ አዳጋችና ለመረዳት ሰፋ ያለ ጊዜን የሚወስድ ሶፍትዌር የተጫነባቸው ናቸው ይሁንና ያለንን መጠነኛ የእንግሊዝኛ አቅም በመጠቀም እኚህን ሶፍትዌሮች በቀላሉ ከ 5 ደቂቃ ባለነሰ መልኩ ከራሳችን ጋር ማዋሀድ እንችላለን፡፡ • የዲሽ ስራ በባህሪው ከቦታ ቦታ መዘዋወርን የሚጠይቅ ስለሆነ ሞተር,ብስክሌት በመግዛት የፈለጉበት ቦታ ድረስ በመሄድ ስራዎን ማከናወን ይችላሉ፡

No comments:

Post a Comment

UFED Cellebrite TOOL CRACK V7.58

Download UFED 7.58 setup https://www.mediafire.com/file/4ctxwl... Download UFED 7.58 keygen https://t.me/habtechzone/45 Download UFED 7.58...