ዲሽ በሚሰራበት ጊዜያት ሊወስዳቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች



                         @በሙለር አይቲ ሶሱሽንስ ተዘጋጅቶ በሀብ ቴክኖሎጅ ሴንተር የቀረበ
  የዲሽ ስራ በሚሰራበት ጊዜያት ሊወስዳቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች  ከምንም ከማንም በላይ ለራሳችን ህይወት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ፡፡ የመሰላሉ ማንኛውም አካል ለአደጋ የሚያጋልጥ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ማረጋገጥ፡፡ አስተማማኝ መሰላሎች በማይገኝበት ወቅት እራስን አደጋ ውስጥ ከማስገባት በፊት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠት መውጣትና መውረድ ለአደጋ እንዳያጋልጠን ነገሮችን አስቀድመን መሬት ላይ መጨረስ
•ለሳህኑ እግር መቀመጫ ቦታ ስንመርጥም ሳህኑ እንዳይንቀሳቀስ ለማጠናከር የምንጠቀምበትን ድንጋይ ወይም ብሎኬት ፡፡ ሌላው መውሰድ ያለብን ጥንቃቄ የቆርቆሮ ጠርዞችን የተመለከተ ሲሆን በምንም አይነት መልኩ እንዲቆርጡን መፍቀድ የለብንም፡፡ በስህተት ማገር ላይ ያልተመታ ቆርቆሮ ላይ በምንረግጥበት ጊዜ የመሰርጎድና ከበድ ያለ የሚንቋቋ ድምፅ ስለሚሰጠን ፈጠን ብለን እግራችንን ማገር ላይ ወደ ተመታው ቆርቆሮ መመለስ ይኖርብናል፡፡
• አንድ አነስ ያለች የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጫ መሳሪያዎችን የያዘች ሳጥን ቢኖረን እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ያስታውሱ ምንጊዜም ቢሆን ለጥንቃቄ ቅድሚያ መስጠት ይኖርብናል፡፡
• በበጋና  ፀሀያማ ወቅት በተለይም ከ ረፋዱ 5፡30 - ቀትሩ 9፡30 በአግባቡና በተዝናኖት እንዳናከናውን ከፍተኛ የሆነ መሰናከል ሊሆኑብን እንደሚችል ግልፅ ነው በመሆኑም በተቻለ መጠን
ከተጠቀሱት ሰአታት ውጭ ባሉት ጊዜያት ስራችንን በአግባቡና በተረጋጋ መንፈስ ማድረግ ይሮርብናል፡፡አለባበሳችን ደግሞ ስንመጣ እግራችንን እንደፈለግን የሚያንቀሳቅሱንን ሱሪዎችንና (እንደ ቱታ ያሉ) በቀለማቸው ሙቀትን የማይስቡ (ከጥቁር ከነጭ ውጭ የሆኑ) ነፀብራቅን የማይፈጥሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ጫማዎቻችን የታችኛው ሶላቸው በደንብ መሬት መቆንጠጥ የሚችልና ሙቀት
አዝልቀው የማያስገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡፡፡

No comments:

Post a Comment

UFED Cellebrite TOOL CRACK V7.58

Download UFED 7.58 setup https://www.mediafire.com/file/4ctxwl... Download UFED 7.58 keygen https://t.me/habtechzone/45 Download UFED 7.58...